ሱዳን ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ የቀረበውን የዘር ማጥፋት ክስ ውድቅ ማድረጉን ተቀበለች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሱዳን ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ የቀረበውን የዘር ማጥፋት ክስ ውድቅ ማድረጉን ተቀበለች
ሱዳን ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ የቀረበውን የዘር ማጥፋት ክስ ውድቅ ማድረጉን ተቀበለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.05.2025
ሰብስክራይብ

  ሱዳን ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ የቀረበውን የዘር ማጥፋት ክስ ውድቅ ማድረጉን ተቀበለች

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ "ክሱ በአካሄድ ምክንያት ውድቅ መደረጉ የሕግ ጥሰቶች እንደሌሉ እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በዘር ማጥፋት ወንጀል ውስጥ ተሳትፎ እንደሌላት የሚያረጋግጥ ውሳኔ አይደለም” ብሏል።

ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመከታተል ሕጋዊ ስልጣን እንደሌለው በመጥቀስ ጉዳዩን ሰኞ ውድቅ አድርጎታል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ቀደም ሲል ፍርድ ቤቱ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ሁለቱም ወገኖች መስማማት እንዳለባቸው የሚደነግገውን የዘር ማጥፋት ስምምነቱን ክፍል በማንሳት ተቃውማለች።

የሱዳን የባህልና መረጃ ሚኒስትር ካሊድ አሊ በኤክስ ገጻቸው "የሱዳን መንግሥት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በኩል ለአማጺው ፈጥኖ ደራሸ ኃይል በተደረገው ቀጣይነት ባለው ድጋፍ በሱዳን ሕዝብ ላይ ለተፈፀሙት ከባድ ወንጀል ኃላፊነት ያለባቸውን ተጠያቂ ለማድረግ ሁሉንም መንገድ መከተሉን ይቀጥላል" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0