የክህሎት ልማት የሀገሪቱን እምቅ አቅም ለማውጣት ወሳኝ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን ተነገሩ

ሰብስክራይብ

የክህሎት ልማት የሀገሪቱን እምቅ አቅም ለማውጣት ወሳኝ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን ተነገሩ

አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወጣት ነው ያሉት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሠራተኛ ስምሪት እና የገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ሰሎሞን ሶካ፤ የዚህን የሕዝብ ክፍል አቅም መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ከ4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

“አብዛኛዎቹ ክህሎቶች ከኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምሰሶዎች ማለትም ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ላይ ያተኮሩ ናቸው” ብለዋል።

ኢትዮጵያ እጅግ ብዙ የተፈጥሮ ሀብቶች እና ወጣት እና ተሰጥኦ ያለው ሕዝብ እንዳላት የተናገሩት ሚኒስትር ደኤታው፤ በዚህ ሀገራዊ ሀብት ለመጠቀም የክህሎት ልማት ላይ መሥራት መሠረታዊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0