የቅጥር ኤጀንሲዎች በኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ላይ የሚፈፅሙትን በደል እንዲያቆሙ በዮሮዳኖስ የኢትዮጵያ አምባሳደር አሳሰቡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየቅጥር ኤጀንሲዎች በኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ላይ የሚፈፅሙትን በደል እንዲያቆሙ በዮሮዳኖስ የኢትዮጵያ አምባሳደር አሳሰቡ
የቅጥር ኤጀንሲዎች በኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ላይ የሚፈፅሙትን በደል እንዲያቆሙ በዮሮዳኖስ የኢትዮጵያ አምባሳደር አሳሰቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.05.2025
ሰብስክራይብ

የቅጥር ኤጀንሲዎች በኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ላይ የሚፈፅሙትን በደል እንዲያቆሙ በዮሮዳኖስ የኢትዮጵያ አምባሳደር አሳሰቡ

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ጆርዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን በኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መብት እና ጥቅሞች ላይ ያተኮረ ውይይት ከጆርዳን የሠራተኛ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣን አብዱላህ አል ጃቦር ጋር አካሂደዋል፡፡

ኃላፊው በመልማይ ኤጄንሲዎች የሚደርሱ በደሎች ላይ የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ማረጋገጣቸውን በዩናይትድ አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ዮርዳኖስ ውስጥ ከ40-50 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች እንዳሉ ይገመታል ሲል ኤምባሲው ጨምሮ ገልጿል።

ኢትዮጵያ እና ዮርዳኖስ እ.ኤ.አ በ2023 የተፈራረሙትን የሁለትዮሽ የሠራተኛ ሥምምነት ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ወደ ዮርዳኖስ በመጓዝ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0