ኮሜሳ እያደጉ ያሉ ሀገራት ብሪክስን የመሰሉ ለንግድ ምቹ የሆኑ ስብስቦችን መቀላቀላቸውን እንደሚደግፍ አስታወቀ

ሰብስክራይብ

ኮሜሳ እያደጉ ያሉ ሀገራት ብሪክስን የመሰሉ ለንግድ ምቹ የሆኑ ስብስቦችን መቀላቀላቸውን እንደሚደግፍ አስታወቀ

የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ ዋና ጸሃፊ ቺሌሺ ካፕዌፕዌ ይህን ያሉት ሰኞ እለት አዲስ አበባ ተካሂዶ በነበረው የኮሜሳ የግንዛቤ መስጫ መድረክ ከስፑትኒክ አፍሪካ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

“አብዛኞቹ አባል ሀገራቶቻችን የብሪክስ አባል ከሆነችው ቻይና ጋር ብዙ የንግድ ልውውጥ አላቸው፡፡ ኢትዮጵያም በቅርቡ ብሪክስን ተቀላቅላለች፤ ይህም ጥሩ እርምጃ ነው፤ ምክንያቱም በንቃት እየተሳተፉ ያሉ አባል ሀገራት አሉን ማለት ነው፡፡ ይህ እያደጉ ያሉ ሀገራት አብረው እንዲጓዙ እና በንግድ ግኑኝነት ውስጥ ሁሉም አካላት የሚደጋገፉበት ትብብር እና ሕብረት ለመፍጠር ይጠቅማል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ 

ኮሜሳ በቀጣናዊ ትስስር የኢኮኖሚ ብልጽግናን የማምጣት ስትራቴጂ አንግቦ፤ በ1987 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን በአጠቃላይ 21 አባል ሀገራትን አቅፏል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0