የኢትዮጵያ የፊልም ሥራዎች በዓለም አቀፉ የዩሬዥያ ፊልም ፌስቲቫል ላይ የሚቀርቡበትን መንገድ በተመለከተ ውይይት ተካሄደ
12:49 06.05.2025 (የተሻሻለ: 13:34 06.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የፊልም ሥራዎች በዓለም አቀፉ የዩሬዥያ ፊልም ፌስቲቫል ላይ የሚቀርቡበትን መንገድ በተመለከተ ውይይት ተካሄደ
የኢትዮጵያ እና የሩሲያ የፊልም ባለሙያዎች በጉዳዩ ዙሪያ በፑሽኪን የባህል ማዕከል ምክክር አድርገዋል።
ታዋቂው የሩሲያ ፊልም ፕሮዲዩሰር እና የፑሽኪን ማዕከል ዳይሬክተር ሰርጌ ኖቮዚሎቭ በጉዳይ ዙሪያ ከኢትዮጵያ የፊልም እና የባህል ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።
ሀገራቱ በፊልም እና ባህል ያላቸውን አጋርነት ማጠናከር ያለመ እንዲሁም የጋራ የፊልም ፕሮጀክቶችን እና ለተማሪዎች የሚሰጡ ፕሮግራሞችን ያካተተ እንደነበር ከማዕከሉ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ፊልሞች በ "ዩሬዥያ" የፊልም ፌስቲቫል ላይ መቅረባቸው የሀገሪቱን የፊልም ኢንዱስትሪ ለዓለም ለማስተዋውቅ እንደሚረዳ በውይይቱ ላይ መነሣቱ ተነግሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X