የእስራኤል አየር ሀይል በየመን ወደብ ላይ ጥቃት ፈፀመ
22:12 05.05.2025 (የተሻሻለ: 09:44 06.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የእስራኤል አየር ሀይል በየመን ወደብ ላይ ጥቃት ፈፀመ
ጥቃት የተፈፀመበት ሆዴዳ ተብሎ የሚጠራው ወደብ ሲሆን 30 የጦር አውሮፕላኖች ተሳትፈዋል። የኮንክሪት ፋብሪካን እና እቃዎችን ለማውረድ የሚያገለግሉ የመርከቦች መቆሚያን ዒላማ ያደረገ መሆኑ ተዘግቧል።
የአየር ጥቃቱ ከአሜሪካ መንግስት ጋር በቅንጅት እንደተካሄደ ተገልጿል።
የአየር ድብደባው ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ የሃውቲ አማፂያን በቴል አቪቭ ቤን ጉሪዮን አየር ማረፊያ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ የተካሄደ ነው።
በማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚዘዋወሩ ምስሎች የጥቃቱን ገፅታ ያሳያሉ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X