የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፖርት ሱዳን የአየር ኃይል ሰፈር ላይ ፈጥኖ ደራሹ ሃይል የፈፀመውን "አስከፊ" ጥቃት አወገዘ
17:15 05.05.2025 (የተሻሻለ: 17:34 05.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፖርት ሱዳን የአየር ኃይል ሰፈር ላይ ፈጥኖ ደራሹ ሃይል የፈፀመውን "አስከፊ" ጥቃት አወገዘ
"የአሸባሪው አርኤስኤፍ ሚሊሺያዎች እሁድ ጠዋት በፖርት ሱዳን የሚገኘውን የኦስማን ዲግና አየር ማረፊያ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ፈፅመዋል። ጥቃቱ በበርካታ መጋዘኖች እና በሲቪል አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ጉዳት አስከትሏል" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በሚኒስቴሩ የተሰጡ ቁልፍ መግለጫዎች፦
⦁ ጥቃቱ የአርኤስኤፍ አማፂያን ሱዳንን ለማተራመስ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን እና አገልግሎቶችን በማጥቃት የሚያደርጉትን ቀጣይነት ያለው ጥረት አካል ነው ፤
⦁ ዓለም አቀፍ ህግና ደንቦችን የሚጥስ ነው ፤
ሚኒስቴሩ የፈጥኖደራሹ ሃይል እና በቀጠናው የሚገኙ ደጋፊዎቹ ተጨማሪ ጥቃቶችን ለማቀድ የጦር መሳሪያ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና ዕቅድ እንዳይኖራቸው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል።
ፀረ-አውሮፕላኖች በርካታ የፈጥኖ ደራሹ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መጥተው ጥለዋል። የሱዳን ጦር ሃይሎች ቃል አቀባይ እንዳሉት ጉዳቱ 'ውስን' ሲሆን በጥቃቱ የተጎዳ ሰው የለም።
ምስል ከማህበራዊ የትስርር ገፆች
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X