በኬንያ ፕሬዝዳንት ላይ የጫማ ጥቃት የሰነዘሩ ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
15:41 05.05.2025 (የተሻሻለ: 16:04 05.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኬንያ ፕሬዝዳንት ላይ የጫማ ጥቃት የሰነዘሩ ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ፖሊስ ዊሊያም ሩቶ እሁድ እለት በሚጎሪ ካውንቲ የሕዝብ ንግግር እያደረጉ በነበረበት ወቅት የተፈጠረው ክስተት ድንገት የሆነ ወይስ ታቅዶ የተፈፀመ እንደሆነ እየመረመረ መሆኑን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የቅድሚያ መረጃዎች ጥቃቱ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ እና የታሰበ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
ክስተቱ በሰፊው ሕዝባዊ ውግዘት ገጥሞታል።
የናይሮቢ ካውንቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ኤስቴር ፓሳሪስ "በፕሬዳንቱ ላይ ጫማ መወርወር ተቃውሞ አይደለም፤ ትንኮሳ ነው። በሚጎሪ የተከሰተውን አሳዛኝ ክስተት አጥብቄ አወግዛለሁ። ይህ በቀስቃሽ ግለሰብ የተፈፀመው አሳፋሪ ድርጊት የኬንያውያንን እሴት እና ምኞት አያንጸባርቅም" ሲሉ በአኬክስ ገጻቸው ተናግረዋል።
ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘው ምስል ፕሬዝዳንቱ በጫማው የተመቱበትን ቅፅበት ያሳያል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X