ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ የተሠሩ የክህሎት ውጤቶችን ወደፊት ወደ ውጭ መላክ እንደምትፈልግ ባለሥልጣኑ ተናገሩ
14:35 05.05.2025 (የተሻሻለ: 14:54 05.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ የተሠሩ የክህሎት ውጤቶችን ወደፊት ወደ ውጭ መላክ እንደምትፈልግ ባለሥልጣኑ ተናገሩ
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ደኤታ
ተሻለ በሬቻ "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ከሚገኘው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ቃል ኢትዮጵያ ክህሎት መር የሥራ ፈጠራን እየተከተለች እንደሆነ ተናግረዋል።
በውድድሩ ላይ የቀረቡት ፈጠራዎች የሀገሪቱን የተለያዩ ዘርፎች የሚያግዙ እንደሆነም ነው የጠቆሙት።
"በውድድሩ አብዛኞቹ የቀረቡት ቴክኖሎጂዎች እና በተማሪዎች እና ሰልጣኝች የቀረቡት ምርቶች የግብርናውን፣ የማዕድን፣ የቱሪዝም እና ሌሎች ዘርፎችንም ውጤታማነት እና ምርታማነት የሚጨምሩ ናቸው" ብለዋል።
አክለውም በኢትዮጵያ ክህሎት እና ፈጠራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን እና ይህም የሀገሪቱን ምርታማነት እንደሚያሳድግ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X