ኢትዮጵያ የጣና ሐይቅ ደሴቶች በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ የሚያስችል ሰነድ ለዩኔስኮ ላከች
20:34 04.05.2025 (የተሻሻለ: 20:54 04.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የጣና ሐይቅ ደሴቶች በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ የሚያስችል ሰነድ ለዩኔስኮ ላከች
ሰነዱ በባለሙያዎች ተገምግሞ፣ አስተያየት እና ተጨማሪ ማስረጃዎችን በማካተት የዩኔስኮን ጥብቅ መሥፈርቶች አሟልቶ እንደተላከ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
ሂደቱ የአማራ ክልልን የባህል ቅርሶችና ቱሪዝም ለማስተዋወቅ እየተደረገ ያለው ጥረት አካል ነው ተብሏል።
ቤሮው ከኢትዮጵያ የቅርስ ባለሥልጣን ጋር በመሆን የጣና ሐይቅ ገዳማት፣ አድባራት እና የተፈጥሮ ሃብቶችን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ሢሠራ ቆይቷል።
የጣና ሐይቅ ደሴቶች ቀደም ሲል የዓለም የብዝሃ ሕይወት ቅርስ ቦታ የሚል እውቅና አግኝተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X