ኢትዮጵያ በተኪ ምርቶች ያስመዘገበችው ስኬት አበረታች ነው ተባለ

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ በተኪ ምርቶች ያስመዘገበችው ስኬት አበረታች ነው ተባለ
ኢትዮጵያ በተኪ ምርቶች ያስመዘገበችው ስኬት አበረታች ነው ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.05.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በተኪ ምርቶች ያስመዘገበችው ስኬት አበረታች ነው ተባለ

መንግሥት ሀገር ውስጥ ለሚመረቱ ምርቶች ቅድሚያ በመሥጠት ግዢ እየፈፀመ ነው ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ደኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ይህም አምራቾች ተኪ ምርትን እንዲያመርቱ እያበረታታቸው ነው ብለዋል።

በዚህም በዘጠኝ ወር ውስጥ ብቻ 3.1 ቢሊዮን ዶላር ሀገር ውስጥ ማስቀረት እንደተቻለ ገልጸዋል።

አክለውም 96 የሚጠጉ ምርቶችን በመለየት በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ግዜ ውስጥ ለመተካት ስትራቴጂ መነደፉን አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0