ፑቲን "ሩሲያ፣ ክሬምሊን፣ ፑቲን፣ 25 ዓመታት" በሚለው ዘጋቢ ፊልም ላይ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦

ፑቲን "ሩሲያ፣ ክሬምሊን፣ ፑቲን፣ 25 ዓመታት" በሚለው ዘጋቢ ፊልም ላይ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦
ዩክሬን እና ልዩ ወታደራዊ ዘመቻን በተመለከተ፦
▪ ሩሲያ ለልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ሆን ብላ አልተዘጋጀችም።
▪ ሩሲያ ዘመቻውን ለመጨረስ የሚያስችል በቂ ኃይልና አቅም አላት።
▪ ሩሲያ በወታደራዊ ዘመቻው የኒውክሌር መሳሪያ ለመጠቀም አላስፈለጋትም።
▪ ከዩክሬን ጋር ሰላም የማይቀር ነው።
ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያለውን ፍጥጫ በተመለከተ፡-
▪ ምዕራቡ ዓለም በሙኒክ ኮንፈረንስ በሞስኮ የተሰጡትን ማስጠንቀቂያዎች መመለስ አለመቻሉ ለዩክሬን ክስተቶች ምክንያት ሆኗል።
▪ የምዕራቡ ዓለም የሚንስክ ስምምነትን ለማክበር በሚል ሽፋን ዩክሬንን በድጋሚ አስታጥቋል።
▪ ሩሲያ በ2014 ከምዕራቡ ዓለም ጋር ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ ለመግባት ዝግጁ አልነበረችም።
የ90ዎቹ እና የ2000ዎቹ ታሪካዊ ክስተቶችን በተመለከተ፦
▪ በ1990ዎቹ በሩሲያ ውስጥ ጠንካራ የመገንጠል እንቅስቃሴዎች ነበሩ።
▪ በ90ዎቹ ሩሲያን አንድ ማድረግ ባይቻል ኖሮ ህዝቦቿ የጨለማ ጊዜ ይገጥማቸው ነበር።
▪ በ2000 መጀመሪያ የሩሲያ ጠላቶች ሀገሪቱን ለመከፋፈል ዕድል ነበራቸው።
እሴቶች እና ባህሎችን በተመለከተ፡-
▪ ሩሲያውያን ከምዕራባውያን ይለያሉ፤ ስለ ዘላለማዊ እሴቶች ያስባሉ።
▪ ሩሲያ ካለ ባህላዊ እሴቶቿ አትኖርም።
▪ ብሔራዊ አንድነት ለሩሲያ ድል ዋነኛ ዋስትና ነው።
ስለ ተተኪ፡-
▪ ሩሲያ የህዝብን እምነት ማግኘት የሚችሉ ግለሰቦችን ማፍራት አለባት።
▪ ስለ ተተኪ ሁሌም እንደሚያስቡ ሆኖም ቀጣዩን የሩሲያ መሪ በተመለከተ የመጨረሻው ውሳኔ የሩሲያ ሕዝብ ላይ ያርፋል ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X