የእስራኤል አየር ኃይል በሶሪያ "በደርዘን የሚቆጠሩ የመሠረተ ልማት እና የጦር መሣሪያ ማምረቻዎችን" አጠቃ
11:02 04.05.2025 (የተሻሻለ: 11:44 04.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የእስራኤል አየር ኃይል በሶሪያ "በደርዘን የሚቆጠሩ የመሠረተ ልማት እና የጦር መሣሪያ ማምረቻዎችን" አጠቃ
▪ የእስራኤል መከላከያ ኃይል ባወጣው መግለጫ "ፀረ-አውሮፕላን መድፎች እና የምድር-አየር ሚሳኤል ማስወንጨፊያ" በዋነኛነት ኢላማ እንደተደረጉ ገልጿል። ጥቃቱ በ12 የጦር አውሮፕላኖች አርብ ምሽት እንደተፈፀመ አስታውቋል።
▪ በሌላ መግለጫ አምስት የቆሰሉ የሶሪያ ድሩዞች ሌሊቱን ወደ እስራኤል ተወስደዋል።
የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ደማስቆ በሚገኘው የፕሬዝዳንታዊ ቤተ-መንግሥት አካባቢ አርብ እለት ጥቃት ፈፅመዋል። ቴል አቪቭ እርምጃው በሶሪያ ድሩዝ ሕዝቦች ላይ ለሚደርሰው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እንደሆነ ተናግራለች።
የሶሪያ ባለሥልጣናት ጥቃቱን አደገኛ አካራሪ ዕርምጃ ብለውታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X