የቀድሞዋ የኡጋንዳ ዳኛ ብሪታኒያ ውስጥ በዘመናዊ የባርነት ወንጀል ከስድስት ዓመት በላይ እስር ተፈረደባቸው
19:17 03.05.2025 (የተሻሻለ: 19:34 03.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቀድሞዋ የኡጋንዳ ዳኛ ብሪታኒያ ውስጥ በዘመናዊ የባርነት ወንጀል ከስድስት ዓመት በላይ እስር ተፈረደባቸው
የሃምሳ አመቷ የቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ፍርድ ቤት ዳኛ ሊዲያ ሙጋምቤ በኦክስፎርድ ክራውን ፍርድ ቤት ቅጣቱ እንደተላለፈባቸው ፍርድ ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል።
ዳኛዋ ጥፋተኛ የተባሉበት የተለያዩ ክሶች፡-
⦁ የኢሚግሬሽን ህግ ጥሰቶችን ለማመቻቸት ማሴር፣
⦁ ለብዝበዛ የሚደረግ ጉዞን ማመቻቸት፣
⦁ በግዳጅ ጉልበት ማሠማራት
⦁ ምስክሮችን ማስፈራራት።
"ሙጋምቤ ወጣቷ ተጎጂ ለተገቢ ደመወዝ የመሥራት መብቷን አለማወቋን ተጠቅመውበታል። ተጎጂዋ በግዳጅ የቤት ሠራተኝነት እና ነፃ የሕፃናት እንክብካቤ እንድትሰጥ በማድረግ በግልፅ ብዝበዛ እና ማጎሳቆል አድርሰዋል" ይላል መግለጫው።
ተከሳሿ ለተጎጂዋ 16 ሺህ 141 የአሜሪካ ዶላር ካሳ እንዲከፍሉም ፍርድ ቤቱ አዟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X