የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ በድርጅቱ ማሻሻያ ዙሪያ በቅርቡ ለአባል ሀገራት ሀሳቦችን እንደሚያቀርቡ ተገለፀ
13:48 03.05.2025 (የተሻሻለ: 14:04 03.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ በድርጅቱ ማሻሻያ ዙሪያ በቅርቡ ለአባል ሀገራት ሀሳቦችን እንደሚያቀርቡ ተገለፀ
ይህም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንደሚሆን የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ለሚዲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።
እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ የማሻሻያ ሃሳቡ በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ያተኩራል፦
⦁ የሀብት አጠቃቀምን ማሻሻል፣
⦁ ኃላፊነትን መልሶ ማደራጀት፣
⦁ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስርዓት ውስጥ መዋቅራዊ ለውጥ ማድረግ።
አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተመድ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የወጪ ቅነሳን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮግሞችን መጋቢት ወር ላይ ይፋ አድርገዋል። ማሻሻያው የትራምፕ አሜሪካ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምታደርገውን የገንዘብ ድጋፍ እየቀነሰች ባለበት ጊዜ የመጣ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X