በማዕከላዊ ኢትዮጵያ 11 የቱሪስት መዳረሻዎች እየለሙ ነው ተባለ
12:05 03.05.2025 (የተሻሻለ: 12:24 03.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ 11 የቱሪስት መዳረሻዎች እየለሙ ነው ተባለ
የማልማት ሥራው የቱሪስት ፍሰትን ለማሳደግና ዘርፉን ለማነቃቃት ያለመ መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡
በጢያ ትክል ድንጋይ ዙሪያ ሎጆች እና የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑም ተገልጿል።
ባለፉት 9 ወራት ከ447 ሺህ በላይ ቱሪስቶች በክልሉ የሚገኙ መስህቦችን ጎብኝተው 825 ሚሊየን ብር ገደማ መገኘቱን ቢሮውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ክልሉ ፏፏቴዎች፣ ጥብቅ ደኖች፣ ትክል ድንጋዮች እና ዋሻዎችን ጨምሮ በርካታ ተፈጥሯዊ እና ባህላዊ የቱሪስት መስቦችን ይዟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X