ኢትዮጵያ የቡና ቱሪዝም ፓኬጆችን ማዘጋጀት ጀመረች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የቡና ቱሪዝም ፓኬጆችን ማዘጋጀት ጀመረች
ኢትዮጵያ የቡና ቱሪዝም ፓኬጆችን ማዘጋጀት ጀመረች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.05.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የቡና ቱሪዝም ፓኬጆችን ማዘጋጀት ጀመረች

እቅዱ ሀገሪቱ የቡና ምንጭ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ከዘርፉ ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ በማሰብ የተዘጋጀ ነው።

ቡና ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ባለፈ የተለየ ባህላዊ ዋጋ አለው ያሉት የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ፤ መሥሪያ ቤታቸው ከቡና ማሕበራት ጋር በመተባበር ለጎብኚዎች የሚሆኑ ፓኬጆችን እያዘጋጀ እንደሆነ ገልጸዋል።

የቡና በቀላ፣ ለቀማ እና ሁሉንም የቡና ማቀነባበሪያ ሂደቶች እንዲሁም ደማቅ የቡና ባህል ሥነ-ሥርዓቶችን ያካትታል መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ቡና ዘርፍ ከ25 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የኑሮ መሠረት እንደሆነም ተነግሯል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0