ኬንያ ከፈረቃ መብራት ለመዳን ከኢትዮጵያ ተጨማሪ የኤሌትሪክ ኃይል ልትጠይቅ ነው

© telegram sputnik_ethiopiaኬንያ ከፈረቃ መብራት ለመዳን ከኢትዮጵያ ተጨማሪ የኤሌትሪክ ኃይል ልትጠይቅ ነው
ኬንያ ከፈረቃ መብራት ለመዳን ከኢትዮጵያ ተጨማሪ የኤሌትሪክ ኃይል ልትጠይቅ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.05.2025
ሰብስክራይብ

ኬንያ ከፈረቃ መብራት ለመዳን ከኢትዮጵያ ተጨማሪ የኤሌትሪክ ኃይል ልትጠይቅ ነው

እየጨመረ የመጣውን የሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ለሟሟላት እና ሊከሰት የሚችል እጥረትን ለመቅረፍ ከኢትዮጵያ ከ50 እስከ 100 ሜጋ ዋት ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተላለፍ ድርድር መጀመሩን ኬንያ ፓወር አስታውቋል።

ይህም ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ባለው ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ወቅት የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ለማረጋጋት ያለመ ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ 2022 በተፈረመው የ25 ዓመት ስምምነት መሠረት በኪሎ ዋት 6.5 ሳንቲም ዶላር እያስከፈለች ለኬንያ 200 ሜጋ ዋት ታቀርባለች።

ኬንያ የጠየቀችው ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደሚገኝ ተዘግቧል። ስምምነቱ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ የኬንያ ሚዲያ ጨምሮ ገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0