የኬንያ ፓርላማ አባል ናይሮቢ ጎዳና ላይ ተገደሉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኬንያ ፓርላማ አባል ናይሮቢ ጎዳና ላይ ተገደሉ
የኬንያ ፓርላማ አባል ናይሮቢ ጎዳና ላይ ተገደሉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.05.2025
ሰብስክራይብ

የኬንያ ፓርላማ አባል ናይሮቢ ጎዳና ላይ ተገደሉ

ቻርለስ ዌሬ ሚያዝያ 22 ምሽት በተጨናነቀ መስቀለኛ መንገድ ላይ መኪናቸው ውስጥ በጥይት ተመትተው ተገድለዋል።

ፖሊስ አንድ ሞተር ሳይክል ከመኪናው ጎን በመቆም ከዛም ተሳፋሪው ጠጋ ብሎ ተኩስ ከከፈተ በኋላ በሞተር ሳይክሉ እንዳመለጠ የሚጠቁም ማስረጃ አግኝቷል።

በመኪናው ውስጥ የነበሩት ጠባቂ እና ሹፌር ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ተገልጿል።

ፖሊስ ዝርዝር ማብራሪያ ሳይሰጥ ግድያውን "የታቀደ" ሲል ገልጾታል።

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ለማቆም "የተሟላ" ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

እ.ኤ.አ 2022 በኦሬንጅ ዴሞክራቲክ ንቅናቄ ሥር የተመረጡት ዌሬ የካሲፑል የምርጫ ክልል ተወካይ ናቸው። የፓርቲው መሥራች ራይላ ኦዲንጋ "የሀገሪቱ ጀግና ልጅ" ሲሉ አወድሰዋቸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0