ዩክሬን ወደ 2006 ድንበሯ መመለስ አትችልም ሲሉ ማርኮ ሩቢዮ ተናገሩ
11:42 02.05.2025 (የተሻሻለ: 12:04 02.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዩክሬን ወደ 2006 ድንበሯ መመለስ አትችልም ሲሉ ማርኮ ሩቢዮ ተናገሩ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሽንግተን የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት ቁርጠኛ ናት ብለዋል። ሆኖም በሞስኮ እና ኪዬቭ መካከል አሁንም ሰፊ የአቋም ልዩነት መኖሩን ተናግረዋል።
"አንዱ ወይም ሁለቱም ወገኖች ዝግጁ መሆን ካልቻሉ ፕሬዝዳንቱ በከፈተኛ የመንግሥት ደረጃ ለጉዳዩ ምን ያህል ተጨማሪ ጊዜ መስጠት እንዳለባቸው መወሰን ይኖርባቸዋል" ብለዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ጋር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ፍላጎት እንዳላቸው ማረጋገጣቸውን ክሬምሊን ሚያዝያ 18 ቀን ማስታወቁ ይታወሳል። የክሬምሊን ተወካይ ኪዬቭ ዝግጁነቷን መግለጽ ቢኖርባትም፤ ሞስኮ እስካሁን ምንም ዓይነት ምልክት እንዳልደረሳት ገልጸዋል፡፡ የዩክሬን ባለስልጣናት ከሩሲያ ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶች ላይ የጣሉትን እገዳ በቅርቡ እንደሚያነሱ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X