በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን "አስደናቂ" ሲሉ ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን "አስደናቂ" ሲሉ ገለፁ
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን አስደናቂ ሲሉ ገለፁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.05.2025
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን "አስደናቂ" ሲሉ ገለፁ

አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በማዕከሉ ጉብኝት አካሂደዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ ዲፕሎማሲ መሪ ከጉብኝቱ በኋላ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ በተቋሙ የተመለከቱት ሥራ አስደናቂ መሆኑን ገልጸዋል።

ማካካስ ከማይቻሉ ነገሮች መካከል አንዱ ጊዜ ነው ያሉት አምባሳደሩ፤ አገልግሎቱ ሰዎች ሰዓታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የሚያስችል እንደሆነ መመልከታቸውን ተናግረዋል።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ጣሪያ ሥር 12 የፌዴራል መንግሥት ተቋማትን አቅፎ 40 የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎቶችን መስጠት እንደጀመረ መገለፁ የሚታወስ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0