ዛምቢያ የኢትዮጵያን ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መተግበር እንደምትፈልግ ገለፀች
13:38 01.05.2025 (የተሻሻለ: 13:54 01.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዛምቢያ የኢትዮጵያን ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መተግበር እንደምትፈልግ ገለፀች
የኢትዮጵያ ፕሮጀክት በሀገር ውስጥ የበለፀገ መሆኑ የዛምቢያን ትኩረት እንደሳበ የስማርት ዛምቢያ ብሔራዊ አስተባባሪ ፐርሲ ቺንያማ አዲስ አበባ ተካሂዶ በነበረው የአፍሪካ ኢኖቬሽን ፎረም ላይ ተናግረዋል።
አክለውም ሉሳካ የግዙፍ ኩባንያዎችን ሶፍትዌር ሀገር ውስጥ በሚበለጽጉ ስርዓቶች እየቀየረች እንደሆነ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እስከ ፈረንጆቹ 2030 90 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንን ለመመዝገብ ወጥኗል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X