መንግሥት በያዝነው ዓመት በሁሉም የኢኮኖሚ መስኮች ከ3 ሚሊዮን በላይ ሥራዎች ተፈጥረዋል አለ
12:33 01.05.2025 (የተሻሻለ: 12:54 01.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱመንግሥት በያዝነው ዓመት በሁሉም የኢኮኖሚ መስኮች ከ3 ሚሊዮን በላይ ሥራዎች ተፈጥረዋል አለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
መንግሥት በያዝነው ዓመት በሁሉም የኢኮኖሚ መስኮች ከ3 ሚሊዮን በላይ ሥራዎች ተፈጥረዋል አለ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በዓለም ለ136ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀንን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት የገለፀው ነው።
መሥሪያ ቤቱ ፈጠራና ፍጥነት የታከለበት የክህሎት ግንባታ ቀጣይነት ላለው የሥራ እድል ፈጠራና ዋስትና ወሳኝ ነው ብሏል።
መንግሥት ከተለያዩ ሀገራት ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት ከ340 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር የሥራ እድሎች እንደተፈጠሩም ተገልጿል። በተጨማሪም ከ45 ሺህ በላይ የርቀት ሥራዎች (remote jobs) ተፈጥረዋል ሲል አገልግሎቱ አስታውቋል።
"ኢትዮጵያ የዓለም የሠራተኞች ቀንን የምታከብረው የኢንዱስትሪ ሰላምን፣ የሥራ ላይ ደኅንነትንና የሠራተኞችን ክሕሎት ማሳደግን ልዩ ትኩረት በመስጠት ነው፡፡ ወደ ብልጽግና የሚደረገዉ ጉዞ ያለ ኢንዱስትሪ ሰላም፣ ያለ ሠራተኞች የሥራ ላይ ደኅንነት እና ዘመኑ የሚጠይቀዉን ክሕሎት ለሠራተኛዉ ሳያስታጥቁ የሚታሰብ አይደለም" ሲል የኮሚኒኬሽን ቤሮው ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X