የሚኒስትሮች ምክር ቤት የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው አስተላለፈ
11:17 01.05.2025 (የተሻሻለ: 11:34 01.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሚኒስትሮች ምክር ቤት የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው አስተላለፈ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው አስተላለፈ
ድንጋጌው የዜጎችን የመሬት ይዞታ የማግኘትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ መልኩ ለውጭ ዜጎች ህጋዊ አሠራር የሚዘረጋ ነው ተብሏል።
እንደ ምክር ቤቱ ገለጻ ረቂቅ አዋጁ የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የውጭ ካፒታል እንዲያመጡ ለማበረታታት፣ የቤት ልማት እና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማነቃቃት፣ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና አቅርቦት ሚዛን ለማስጠበቅ እና ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
ምክር ቤቱ በሕጉ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
44ኛው መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው አስፈጻሚው አካል በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X