የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ቁጥር በእጥፍ ጨመረ
15:29 30.04.2025 (የተሻሻለ: 15:44 30.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ቁጥር በእጥፍ ጨመረ
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 2 ሺህ 700 በላይ ቱሪስቶች ፓርኩን ጎብኝተዋል።
በተጨማሪም ከቱሪስቶች የመግቢያ ትኬትና ከፊልም ቀረጻ ሥራ ግማሽ ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገቢ ተሰብስቧል፡፡ በፓርኩ አዋሳኝ ወረዳዎች በኢኮ ቱሪዝም የተደራጁ ማሕበራት ለጎብኚዎች ባቀረቡት አገልግሎት ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘታቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
የብሔራዊ ፓርኩን ብዝሀ ህይወት የበለጠ ለመጠበቅ እና ከሕገ-ወጥ አደን ለመታደግ የአምስት ዓመት ስትራቴጂ ተቀርፆ ወደ ሥራ ተገብቷል።
412 ስክዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ዋልያ፣ ቀይ ቀበሮ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ እንዲሁም የሌሎች ብርቅዬ የዱር እንስሳትና አእዋፋት መገኛ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X