ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት በኒውክሌር ኢንጂነሪግ የመጀመሪያ ዲግሪ መስጠት ልትጀምር ነው
12:18 30.04.2025 (የተሻሻለ: 12:54 30.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት በኒውክሌር ኢንጂነሪግ የመጀመሪያ ዲግሪ መስጠት ልትጀምር ነው
የትምህርት ፕሮግራሙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ፣ ከቻይና መንግሥት ቺኒጉዋ ዩኒቨርስቲ እና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጋር በደረሠው ስምምነት መሠረት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
ዓላማው በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሳይንስና ምርምርን ማስፋት፣ በዘርፉ ኢትዮጵያዊ ኢንጂነሮችን ማፍራት እንዲሁም ለአፍሪካ አባል ሀገራት የትምህርትና ስልጠና ማዕከል መፍጠር እንደሆነ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ "ኢትዮጵያ ፕሮግራሙን ለመስጠት የተመረጠችው ዘርፈ ብዙ ድርድሮች ተደርገውና የማስተናገድ አቅሟ ከግምት ውስጥ ገብቶ ነው" ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እና የቻይናው ቺኒጉዋ ዩኒቨርስቲ ትብብር 10 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን አስተማሪዎች ለ6 ወር በቻይና ቺኒጉዋ ዩኒቨርስቲ ይሰለጥናሉ ተብሏል፡፡ ከዛም ለአፍሪካ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ አባል ሀገራት ኢትዮጵያ ውስጥ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም መስጠት እንደሚጀምሩ ተነግሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X