በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር “ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ወደብ አልባ ሳትሆን በመሬት የተሳሰረች ሀገር ናት” ሲሉ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopiaበፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር “ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ወደብ አልባ ሳትሆን በመሬት የተሳሰረች ሀገር ናት” ሲሉ ተናገሩ
በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር “ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ወደብ አልባ ሳትሆን በመሬት የተሳሰረች ሀገር ናት” ሲሉ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.04.2025
ሰብስክራይብ

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር “ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ወደብ አልባ ሳትሆን በመሬት የተሳሰረች ሀገር ናት” ሲሉ ተናገሩ

ሀገሪቱ 95 በመቶ የሚሆነውን የገቢ እና ወጪ ንግዷን የኢትዮ-ጅቡቲን የባቡር መስመር ተጠቅማ እንደምታሳልጥ አምባሳደሩ ጀማል በክር ለፓኪሰታን ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ የማጓጓዝ ሂደቱ ከግማሽ ቀን በላይ እንደማይፈጅም ነው የጠቆሙት።

አክለውም የኢትዮጵያ 7 ደርቅ ወደቦች የሎጂስቲክስ ዘርፉን ማነቆዎች ቀርፈዋል ብለዋል፡፡

አምባሳደሩ የካራቺን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት በጎበኙበት ወቅት የፓኪስታን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንዲሁም በመጪው ግንቦት 4 እና 5 በሚካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0