ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 60 ሺህ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በላሙ ወደብ በኩል ማስገባቷን አስታወቀች
15:59 29.04.2025 (የተሻሻለ: 16:14 29.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 60 ሺህ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በላሙ ወደብ በኩል ማስገባቷን አስታወቀች
ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የምትልከው የወጪ ንግድ ከ57 ሚሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል። በተጨማሪም ለጎረቤቷ የምትሸጠው የኤሌክትሪክ ኃይል እየጨመረ መምጣቱን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
በሌላ በኩል ኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የምትልከው የወጪ ንግድ ዋጋ 119 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ተጠቁሟል።
149 የሚሆኑ የኬንያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተሠማርተው ኢንቨስት እያደረጉ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ-ኬንያ የቢዝነስ ፎረም ከቀናት በፊት ናይሮቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተካሂዷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X