በስፔን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መበላሸቱን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ
14:25 29.04.2025 (የተሻሻለ: 16:14 29.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በስፔን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መበላሸቱን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ
የስፔን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በመላው አውሮፓ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ኤሌክትሪክ ኃይል ማጣታቸውን ተከትሎ አዋጁን ማውጣቱን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ ስፔንን፣ ፖርቱጋልን፣ ቤልጄምን እና የተወሰነ የፈረንሳይ ክፍል መሸፈኑ ተነግሯል። በተለይም ማድሪድ እና ባርሴሎና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች ማቋረጥ እና በማድሪድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የኃይል መቋረጥ ሪፖርት ተደርጓል።
በመላው ስፔን የሚገኙ ሱፐር ማርኬቶች ተዘግተዋል። እንደ ምክንያት የጠቀሱትም በድንጋጤ የተዋጡ ዜጎች አስቤዛ ለማከማቸት መደርደሪያዎቻቸው ባዶ በማስቀረታቸው ነው።
የፖርቱጋል ባለስልጣናት እንዳሉት ችግሩ የተከሰተው በስፔን የኤሌክትሪክ ኃይል ስርዓት ላይ በተከሰተ "እንግዳ የአየር ሁኔታ ክስተት" ምክንያት ሲሆን ምንም አይነት የሳይበር ጥቃት ምልክት የለም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/ © telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
