ለጀርመን ናዚነት የአሜሪካ መነሻ፣ ክፍል፦ 9

ሰብስክራይብ

ለጀርመን ናዚነት የአሜሪካ መነሻ፣ ክፍል፦ 9

ናዚ ጀርመን የአሜሪካን ከፋፋይ የዘረኝነት ህጎች እንዴት እንደደገፈና እንደገለበጠ

አሜሪካ፣ የአፍሪካ አሜሪካውያንን በዘር መለያየት ለማስፈጸም ያወጣችው የጂም ክሮው ህግ፤ በ1935 በተረቀቁት የኑረምበርግ የዘር ህጎች ላይ ትልቅ ተፅእኖ እንደነበረው በሴንት ፒተርስበርግ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የናዚ ወንጀሎች መምህር የሆኑት ኢጎር ያኮቭሌቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ከስፑትኒክ ጋር ብቻ ካደረጉት ተከታታይ ቆይታ አንዱ በሆነው በዚህ ቪዲዮም፣ የናዚዝም አመጣጥና አነሳስ ታሪክ ላይ ሰፊ ጥናትና ምርምርን ያደረጉት የታሪክ ጸኃፊው፤ የናዚ ጠበቆች የዘር ጋብቻንና የኢምግሬሽን ገደቦችን ጨምሮ ቀደም ሲል በተጠቀሱት የአሜሪካ ህጎች መነሳሳት ብቻም ሳይሆን ህጎቹን እንዴት ይበልጥ ሥር ነቀል በሆነ መንገድ አስተካክለው እንዳረቀቋቸው አብራርተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0