ሩሲያ እና ሶማሊያ የአፍሪካ ቀንድ የሽብር ስጋትን ለማስወገድ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ሞስኮ ገለጸች
18:05 28.04.2025 (የተሻሻለ: 18:24 28.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ሶማሊያ የአፍሪካ ቀንድ የሽብር ስጋትን ለማስወገድ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ሞስኮ ገለጸች
የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚካኤል ቦግዳኖቭ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ጋር የተነጋገሩ ፤ ሲሆን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ፊኪ መወያየታቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ሞስኮ እና ሞቃዲሾ የንግድ ፣ ኢኮኖሚ ፣ ሰብአዊ እርዳታ እና ሌሎች ዘርፎችን ጨምሮ የሁለትዮሽ ሁለገብ ትብብራችውን ለማሳደግ ያላቸውን ፍላጎት አረጋግጠዋል በማለት መግለጫው አስረድቷል።
"የፖለቲካ ውይይቱን ለማጠናከር ስምምነት ላይ ተደርሷል" ሲል አከሎም መግለጫው ይነበባል።
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ቢሮ ቦግዳኖቭ በመጪው የሩሲያ-አረብ ሊግ ጉባዔ ላይ እንዲሳተፉ ከፑቲን ለሞሃሙድ የተደረገውን ይፋዊ ግብዣ ማስተላለፋቸውን አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X