ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ሁሌም ዝግጁ ነች ሲሉ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ

ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ሁሌም ዝግጁ ነች ሲሉ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ
"ኪየቭ እስካሁን ድረስ ለድርድር ዝግጁ መሆኗን አላሳየችም" በማለት ሰርጌይ ላቭሮቭ ከብራዚል ኦ ግሎቦ ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቃለ-ምልልስ ወቅት ተናገሩ።
የዩክሬን ባለስልጣናት "ሰላማዊ የፖለቲካ ፍላጎት እና ጦርነቱን የማስቆም አቅም" እንደሌላቸው የሩሲያው ከፍተኛ ዲፕሎማት አስረድተዋል። እንደማስረጃም በኃይል ማመንጫ ተቋማት ላይ ጥቃት ላለመፈፀም የተጣለውን የ30 ቀናት እገዳ እና የትንሳኤ በዓልን የ30 ሰዓት የተኩስም አቁም አለማከበራቸው ጠቅሰዋል።
የላቭሮቭ በቃለ-ምልልሳቸው ወቅት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፦
⦁ ሞስኮ ዩናይትድ ስቴትስ በዩክሬን ግጭት ላይ ያላትን አቋም ይበልጥ እያወቀች እንደሆነ ይሰማታል፤
⦁ ይህ ግንዛቤ ዋሽንግተን ከኪየቭ እና ከአውሮፓ ሀገራት ጋር በምታደርገው ውይይት ሊረዳት ይችላል ፤
⦁ አሁን ያለው የአሜሪካ አስተዳደር የችግሩን ዋና መንስኤ ለመረዳት ይፈልጋል ፤ ዩክሬንን ማስታጠቅ እና ኔቶን እንድትዋሃድ ግፊት ሲያደርግ ከነበረው የባይደን የትኩረት አቅጣጫ በተለየ፤
⦁ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ለሩሲያ አቻቸው የፓሪሱን የሚያዝያ 9 ውይይት ውጤት አሳዉቀዋቸዋል።
⦁ የአውሮፓ ህብረት ፍትሃዊና ዘላቂ ሰላም ከመፍጠር ይልቅ ለክብሩ ቅድሚያ ይሰጣል፤ "ከሞስኮ ሽንፈት በስተቀር ምንም ነገር አይፈልግም"፤
⦁ የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የሚሰጠውን ድጋፍ ማቋረጡ "ስትራቴጂካዊ ብቃቱ ማነሱን" እንደሚያመለክት ያምናል፤
⦁ ብራስልስ ለኪየቭ የጦር መሳሪያ በማቅረብ፣ ወታደራዊ ቡድኖችን በማሰልጠን እና የሞስኮን ማስጠንቀቂያዎች ችላ በማለት የሰላም ውይይቶችን አሳንሶ እያየ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X