ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያተኮረ የትምህርት ዘርፍ ትብብር እንደምትሻ ገለጸች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያተኮረ የትምህርት ዘርፍ ትብብር እንደምትሻ ገለጸች
ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያተኮረ የትምህርት ዘርፍ ትብብር እንደምትሻ ገለጸች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.04.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያተኮረ የትምህርት ዘርፍ ትብብር እንደምትሻ ገለጸች

የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሽኔ ከኢኖቬሽን አፍሪካ 2025 የሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሩሲያ በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ ኢንቨስት እንድታደርግ ጠይቀዋል፡፡

“ሩሲያ ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የትምህርት እድል ከሚሰጡ ሀገራት ቀዳሚዋ ነች፡፡ በአዲሱ የዓለም ስርዓት ሀገራት ሰዎችን እንዲያሰለጥኑ ብቻ ሳይሆን ቴክኖሎጂዎችንም እንዲያጋሩ እንፈልጋልን” ብለዋል፡፡

ባለስልጣኑ ሀገራት አፍሪካን መርዳት ያለባቸው በኢንቨስትመንት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር መሆኑን ያስረዱ ሲሆን የብሪክስ አባል ሀገራትም ይህንን መስመር እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

"ተመራማሪዎቻችን መተባበር አለባቸው። አፍሪካ ውስጥ ቴክኖሎጂን በማልማት ወደ ብሪክስ አባል ሀገራት ገበያ ማስፋፋት አለባቸው" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አክለውም በብሪክስ ማዕቀፍ የሚደረገው የትምህርት ዘርፍ ትብብር እየተጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

"በብሪክስ ውስጥ ያለው ጅማሮ ጥሩ ነው። በዩኒቨርሲቲዎች፣ በትምህርት እና በመሰል ጉዳዩች ላይ እንዴት መተባበር እንደሚቻል በመወያየት ላይ ነን" ሲሉ አብራርተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0