ኢትዮጵያ በአይኤምኤፍ የ3.4 ቢሊየን የብድር ፕሮግራም ዙሪያ የምታካሄደውን ግምገማ በዚህ ሳምንት በስምምነት ለማጠናቀቅ ትጠብቃለች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በአይኤምኤፍ የ3
ኢትዮጵያ በአይኤምኤፍ የ3 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.04.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በአይኤምኤፍ የ3.4 ቢሊየን የብድር ፕሮግራም ዙሪያ የምታካሄደውን ግምገማ በዚህ ሳምንት በስምምነት ለማጠናቀቅ ትጠብቃለች

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ልዑክ ለአይኤምኤፍ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የብድሩን ሶስተኛ ዙር አፈጻጸም አስመልክቶ በዋሽንግተን ሪፖርት አቀርቧል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ እዩብ ተካልኝ የቅድሚያ ስምምነት በያዝነው ሳምንት ይደረሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል። ቦርዱ ግምገማውን በሰኔ ወር ሊያጸድቀው እንደሚችል ጠቁመዋል። ውሳኔው በብድር ፕሮግራሙ ሥር ለሚደረገው ክፍያ አስፈላጊ እርምጃ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

ሚኒስትር ዲኤታው አክለውም ሀገሪቱ የእዳ ሽግሽግን በተመለከተ በመጪው ሰኔ ከአበዳሪዎቿ ጋር ድርድር ማድረግ ትጀምራለች ብለዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ650 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከዓለም ባንክ ሊያገኝ ነው፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት የሚደረገው የመጀመሪያ ዙር የ350 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ባንኩ ባልተመለሰ ብድር ምክንያት ያጋጠሙትን የፋይናንስ ተግዳሮቶች ለማቃለል ትልቅ እገዛ ያደርጋል መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0