ኢትዮጵያ ለብሪክስ አባል ሀገራት ባህሏንና እና ኪነ ጥበቧን ለማስተዋወቅ የምታደርገዉን ጥረት ሩሲያ ትድግፋለች ሲሉ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን አስታወቁ
14:53 28.04.2025 (የተሻሻለ: 15:34 28.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለብሪክስ አባል ሀገራት ባህሏንና እና ኪነ ጥበቧን ለማስተዋወቅ የምታደርገዉን ጥረት ሩሲያ ትድግፋለች ሲሉ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን አስታወቁ
የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ እና ከአምባሳደሩ በባህል፣ በኪነ ጥበብ እና በስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመሥራት መነጋገራቸውን ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ትሥሥር ገፁ አስነብቧል።
በውይይታቸው ኢትዮጵያ የብዝሃ ባህል ባለቤት እና ታሪካዊ ሀገር እንደመሆኗ ከሩሲያ መንግሥት ጋር በነዚህ ዘርፎች ላይ በትብብር መሥራት አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል።
በቀጣይ የጋራ የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር በሚበጁ ሥራዎች ላይም በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X