የፈጥኖ ደራሹ ሃይሎች ከሱዳን ጦር ጋር 'አዲስ ምዕራፍ ጦርነት' መጀመራቸውን አስታወቁ

ሰብስክራይብ

የፈጥኖ ደራሹ ሃይሎች ከሱዳን ጦር ጋር 'አዲስ ምዕራፍ ጦርነት' መጀመራቸውን አስታወቁ

የፈጥኖ ደራሹ ሃይሎች (አርኤስኤፍ) የዋዲ ሴይዳን አየር ሰፈር ላይ ጥቃት በመፈፀም የጦር አውሮፕላኖችን፣ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና የጦር መሳሪያ ማከማቻዎችን ኢላማ በማድረግ ጥቃት ማድረሳቸው ከተዘግበ በኋላ የሃይሉ አዛዥ አማካሪ ፓሻ ታቢክ መግለጫ ሰጥተዋል።

ታቢክ በቀጣዮቹ ቀናት "የቡርሃን ሚሊሻዎች እና አሸባሪ ቡድኖች" ብለው በጠሯቸው የሱዳን ጦር  ስትራቴጂካዊ ስፍራዎች ላይ ከባድ ጥቃቶች እንደሚፈፀሙ እና ፖርት ሱዳን ቀጣዩ ዒላማ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።

አርብ ዕለት በአትባራ በሚገኝ የመጠለያ ማዕከል ላይ አርኤስኤፍ በፈፀመው ጥቃት በትንሹ 11 ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።

"ከቅርብ ወራት ወዲህ በሁሉም የጦር ግንባሮች ላይ በተከታታይ ከደረሰባቸው ሽንፈቶች በኋላ  የአርኤስኤፍ አሸባሪ ሚሊሺያዎች እንዲህ ዓይነቱን የሽብር ስልት መጠቀም ጀምረዋል " ሲል የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በማኅበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቀ አንድ ምስል በዛሬው ዕለት በናይል ወንዝ ግዛት አል-ማካይላብ በርበር ከተማ በሚገኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የተካሄደውን የአርኤስኤፍ ጥቃት ተከትሎ የተከሰተውን የእሳት ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0