ፓኪስታን ከህንድ ጋር ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት የመከላከያ ሚኒስትሩ አስታወቁ
18:05 27.04.2025 (የተሻሻለ: 18:44 27.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፓኪስታን ከህንድ ጋር ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት የመከላከያ ሚኒስትሩ አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፓኪስታን ከህንድ ጋር ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት የመከላከያ ሚኒስትሩ አስታወቁ
"ነገር ግን ህንድ ፓኪስታንን ለመውረር ወይም ለማጥቃት ከሞከረች ተመጣጣኝ ያልሆነ ምላሽ ይጠብቃታል" ሲሉ ካዋጃ መሐመድ ለስፑትኒክ ተናገሩ።የፓኪስታን የመከላከያ ሚኒስትር በመግለጫቸው ያነሷቸው ነጥቦች ፦
⦁ የፓኪስታን-ህንድ ውጥረት ወደ ኑክሌር ልውውጥ የሚያመራ አይመስልም ፤
⦁ ፓኪስታን ጃሙ እና ካሽሚር ውስጥ በሚያዝያ 22 በተፈፀመው የሽብር ጥቃት ላይ ዓለም አቀፍ ምርመራ እንዲደረግ ትጠይቃለች፤
⦁ ፓኪስታን በጥቃቱ ተሳትፋለች የሚሉ ክሶች ማስረጃ የሌላቸው "ባዶ ክሶች" ናቸው፤
⦁ ሩሲያ እና ቻይና ምርመራውን በመቀላቀል ቀውሱን ለመፍታት "አዎንታዊ ሚና መጫወት" ይችላሉ።
26 ሰዎች የሞቱበት የጃሙ እና የካሽሚር የሽብር ጥቃት ተከትሎ የህንድ-ፓኪስታን ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ ህንድ የኤምባሲ ሰራተኞቿን የቀነሰች ሲሆን፣ የሲንደስ ውኃ ስምምነትን ለጊዜው በማገድ አክላም ከፓኪስታን ጋር ያላትን የመጨረሻ ክፍት የመሬት ድንበር ማቋረጫ ዘግታለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X