የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ከ210 ቢሊዩን ብር በላይ መከፋፋሉን መንግስት አስታወቀ
16:07 27.04.2025 (የተሻሻለ: 17:14 27.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ከ210 ቢሊዩን ብር በላይ መከፋፋሉን መንግስት አስታወቀ
እነዚህ የድጋፍ መርሃግብሮች የተደረጉት ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማቃለል ታልሞ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስታውቋል።
የማዳበሪያ አቅርቦትን ለማረጋገጥ ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ለሚደጉመው የሴፍት ኔት ፕሮግራም ፣ ለነዳጅ ድጎማ እና ለህክምና መድሃኒቶች ግዥ ዋና ዋና ፈሰስ የተደረገላቸው ዘርፎች መሆናቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
ድጎማው በተጨማሪም ለቤተሰብ የዕለት ተዕለት ፍላጎቶች ድጋፍ ለመስጠት እና የመንግስት ሰራተኞችን ደመወዝ ለመክፈል ውሏል።