በሞስኮ የግማሽ ማራቶን ውድድር የኢትዮጵያ እና የኬንያ አትሌቶች ድል ተቀዳጁ
14:35 27.04.2025 (የተሻሻለ: 14:54 27.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሞስኮ የግማሽ ማራቶን ውድድር የኢትዮጵያ እና የኬንያ አትሌቶች ድል ተቀዳጁ
ዛሬ ማለዳ በተካሄደው የሩጫ ውድድር ከመላው ዓለም የተዉጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ አትሌቶች ተሳትፈውበት ነበር።
በወንዶች ዘርፍ ኢትዮጵያዊዉ ቴሬሳ ኒያኮላ 21 ኪሎ ሜትሩን በ1 ሰአት ከ1 ደቂቃ 11 ሰከንድ በማጠናቀቅ ያሸነፈ ሲሆን የግሉን የተሻለ ውጤት አስመዝግቧል።
ኬንያዊቷ አትሌት ዳይዚ ጃሙታይ ሩቶ በ1 ሰአት 09 ደቂቃ በማጠናቀቅ የሴቶች ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች።
በሩሲያ የኬንያ አምባሳደር ፒተር ሙቱኩ ማቱኪ በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ አሸናፊዎቹን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።