የኢትዮጵያ መንግሥት ገቢ 134 በመቶ ብልጫ እንዳስመዘገበ ተገለፀ
16:52 26.04.2025 (የተሻሻለ: 17:14 26.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ መንግሥት ገቢ 134 በመቶ ብልጫ እንዳስመዘገበ ተገለፀ
ገዢው የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትናንትና ዛሬ ካካሄደው መደበኛ ስብሰባ በኋላ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው ያለፉት 9 ወራት ጠቅላላ የመንግሥት ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ134 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ገልጿል። የውጭ ብድር ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ወደ 13.7 በመቶ ወርዷል፡፡
ፓርቲው የውጭ ምንዛሬ ክምችት ዕድገት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ203.99 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ብሏል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነቱ እየጨመረ መምጣቱም ተጠቅሷል።