የሩሲያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም በኩርስክ ክልል የዩክሬን ወታደሮች ሽንፈትን በተመለከተ ካቀረቡት ሪፖርት ዋና ዋና ነጥቦች፦

የሩሲያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም በኩርስክ ክልል የዩክሬን ወታደሮች ሽንፈትን በተመለከተ ካቀረቡት ሪፖርት ዋና ዋና ነጥቦች፦
የጄራሲሞቭ ቁልፍ መግለጫዎች፦
◾ በኩርስክ የገቡትን የዩክሬን ኃይሎች ለማስወጣት የተካሄደው ዘመቻ ተጠናቋል። በክልሉ የመጨረሻው ጎርናል መንደር ዛሬ ቅዳሜ ነፃ ወጥቷል።
▪ በኩርስክ ነፃ በወጡ አካባቢዎች ለመደበቅ እየሞከሩ ያሉትን የዩክሬን የጦር ኃይል ወታደሮች ለመለየት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው።
▪ የዩክሬን የጦር ኃይሎች በኩርስክ ከ76 ሺህ በላይ ወታደሮቹን በሞትና በጉዳት አጥቷል።
▪ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከሩሲያ ጦር ጋር በመሆን በጀግንነት ተዋግተዋል።
▪ በሱሚ ክልል የፀጥታ ቀጣና ማቋቋም ቀጥሏል። አራት መንደሮች ነፃ የወጡ ሲሆን ከ90 ካሬ ኪ.ሜ በላይ መሬት በቁጥጥር ሥር ውሏል።
▪ በኩርስክ የሚገኙ 19 መንደሮች ሙሉ በሙሉ ከፈንጂዎች ነጻ ሆነዋል።
የፑቲን ቁልፍ መግለጫዎች፦
▪ በኩርስክ የጠላት ሙሉ ሽንፈት በግንባሩ ሌሎች ወሳኝ ቦታዎች የሩሲያ የጦር ኃይሎች በቀጣይነት ስኬታማ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ሁኔታዎችን ያመቻቻል።
▪ የኪዬቭ አገዛዝ "ቁማር" ሙሉ በሙሉ ከሽፏል።
▪ የኩርስክ ነፃ መውጣት የኪዬቭን ኒዮ-ናዚ አገዛዝ ሽንፈት ያፋጥናል።
▪ ፑቲን በኩርስክ ውጤታማ የነበሩትን የሩሲያ ጦር ክፍሎችን አመስግነዋል።
▪ ኩርስክን ነፃ ላወጡ የሩሲያ ወታደሮች ጀግንነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።