ለሶማሊያ ሰላም እና መረጋጋት የአፍሪካውያን የጋራ ትብብር ወሳኝ እንደሆነ ኢትዮጵያ አስገነዘበች
12:57 26.04.2025 (የተሻሻለ: 13:14 26.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ለሶማሊያ ሰላም እና መረጋጋት የአፍሪካውያን የጋራ ትብብር ወሳኝ እንደሆነ ኢትዮጵያ አስገነዘበች
በአፍሪካ ሕብረት የድጋፍና የማረጋጋት ተልዕኮ በሶማሊያ ሥር ወታደሮች ያዋጡ ሀገራት የሰላም አስከባሪ ኃይሉን ቁጥር በትንሹ በ8 ሺህ ከፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በአጋንዳ የተካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ ባወጡት የጋራ መግለጫ በሶማሊያ እየጨመረ የመጣው የደህንነት ስጋት በሀገሪቱ ስርዓት በመመለስ ረገድ የተገኘውን ስኬት እንዳያከሸፍ መተባበር እንደሚገባ አስረግጠዋል።
በጉባዔው የኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ጂቡቲ እና ሶማሊያ የመከላከያ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል።