የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከብራዚሉ ኤምብራየር ኩባንያ አውሮፕላን ለመግዛት ጥናት እያደረገ እንደሆነ ገለፀ
19:21 25.04.2025 (የተሻሻለ: 19:44 25.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከብራዚሉ ኤምብራየር ኩባንያ አውሮፕላን ለመግዛት ጥናት እያደረገ እንደሆነ ገለፀ
አዲስ አበባ በተካሄደው የኢትዮጵያ አቪየሽን ፎረም ላይ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገለጻ ያደረጉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፤ ለሀገር ወስጥ በረራ ብዙ ተሳፋሪ የሚይዙ አውሮፕላኖችን የመግዛት እቅድ እንዳለ ጠቁመዋል።
"የሀገር ውስጥ በረራ ፍላጎት ጨምሯል። ትላልቅ አውሮፕላኖች ያስፈልጉናል። በአሁኑ ጊዜ ሁለት የአውሮፕላን ሞዴሎችን እየገመገምን ነው። ከእነዚህ አንዱ ሞዴል ኢምብራየር ኤ2 አውሮፕላን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግሥቴ በበኩላቸው ኢምብራየር በኢትዮጵያ ሥራ እንዲጀምር ፍላጎት እንዳለ ገልጸዋል። አክለውም ይህ አህጉሪቱንም የሚጠቅም ነው ብለዋል።