ለጀርመን ናዚነት የአሜሪካ መነሻ፣ ክፍል 8
17:46 25.04.2025 (የተሻሻለ: 18:04 25.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ለጀርመን ናዚነት የአሜሪካ መነሻ፣ ክፍል 8
በአሜሪካ ‘ኡንታሜንች’ የተሰኘውን ብያኔ ማን ፈጠረው ፣ ናዚዎች ለምን እና እንዴት ተገበሩት?
ከናዚ ርዕዮተ ዓለም መሠረቶች አንዱ አርያንስ ከሰው በላይ ናቸው የሚለው እምነት ነው። ‘‘ኡንታሜንች’’ ወይም ‘‘ ከሰዉ በታች’’ የሚል ብያኔንም፣ ሙሉ ሰዎች አይደሉም ብለው የሚያስቧቸውን እንደ አይሁዶች፣ ሮማንያውያን እና የስላቪክ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ለመግለፅ ይጠቀሙ ነበር፡፡
ሆኖም፣ የዚህ ቃል አመጣጥ እና የዘር ተዋረድ ጽንሰ-ሀሳብ ለመጀመሪያ የተፈጠረው በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ነው።
በዚህ ልዩ የስፑትኒክ ተከታታይ ስምንተኛው ቪዲዮ ላይም የናዚዝም ታሪክ ጸሐፊ እና “የዋር ኦፍ አንሂሌሽን” ደራሲ ኢጎር ያኮቭሌቭ ፣ በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ማን እንደፈጠረው እና ማን ታዋቂ እንዲሆን እንዳደረገ ገልፀዋል።