"ወደ ኔቶ መቀላቀል ይችላሉ ብዬ አላስብም"፦ ትራምፕ ከታይም መፅሄት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ስለ ዩክሬን የተናገሯቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
15:23 25.04.2025 (የተሻሻለ: 15:44 25.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"ወደ ኔቶ መቀላቀል ይችላሉ ብዬ አላስብም"፦ ትራምፕ ከታይም መፅሄት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ስለ ዩክሬን የተናገሯቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"ወደ ኔቶ መቀላቀል ይችላሉ ብዬ አላስብም"፦ ትራምፕ ከታይም መፅሄት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ስለ ዩክሬን የተናገሯቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
◾ክሬሚያ በዩክሬን የሰላም ስምምነት መሠረት "የሩሲያ ግዛት ሆና ትቀጥላለች"፤ ዘለንስኪም ይህን ይረዳል፡፡
◾የግጭቱ መነሻ የዩክሬን የኔቶ አባልነት ውይይት በመሆኑ ኪዬቭ ግጭቱን በማስነሳት ተጠያቂ ናት፡፡
◾በዩክሬን ዙሪያ የሚደረገው ድርድር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው፤ ስምምነቱ "በጣም ተቃርቧል"፡፡
◾በፕሬዝዳትነታቸው ጊዜ በዩክሬን ሰላም እንደሚመጣ ያምናሉ፡፡
◾ግጭቱን በአንድ ቀን ውስጥ ማቆም እችላለሁ የሚለው ንግግራቸው ማጋነን እና ምሳሌያዊ አነጋገር እንደሆነ አምነው፤ ግጭቱን ለማቆም ቃል ገብተዋል፡፡
◾በዩክሬን ያለው ግጭት ለረጅም ጊዜ አይቀጥልም ብለዋል፡፡
◾በሞስኮ እና በኪዬቭ መካከል ስምምነት ከተደረሰ አሜሪካ ከዩክሬን እና ሩሲያ ጋር የንግድ ግንኙነት ማድረግ የምትችልበትን ሁኔታ ትገመግማለች።