የኢትዮጵያ አምራች ኢዱስትሪዎች የሚለቁትን የሙቀት ዓማቂ ጋዝ ልቀት ለመቀነስ ያለመ ስምምነት ተፈረመ
13:39 25.04.2025 (የተሻሻለ: 13:54 25.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አምራች ኢዱስትሪዎች የሚለቁትን የሙቀት ዓማቂ ጋዝ ልቀት ለመቀነስ ያለመ ስምምነት ተፈረመ
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፓን አፍሪካ ግሪን ኢነረጂ ጋር በትብብር ለመሥራት መግባባት ላይ ደርሷል።
ድርጅቱ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን የድንጋይ ከሰል የሚተካ ግብዓት ከፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረም ባዮ ማስ እንደሚያመረት ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ ከፍተኛ የድንጋይ ከሰል ከሚጠቀሙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች አንድ ቶን ሲሚንቶ በማምረት ሂደት ከሚለቀቀው የሙቀት ዓማቂ ጋዝ ልቀት ውስጥ 0.03 ቶን የሙቀት ዓማቂ ጋዝ ልቀት ለመቀነስ ዓላማ አለው።
የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግ እና የአምራች ኢንዱስትሪውን አቅም መገንባት ሌላው የስምምነቱ ትኩረት እንደሆነ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።