የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት በቀጣዩ የበጀት ዓመት ወደ 10 በመቶ ዝቅ እንደሚል የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ አስታወቀ
12:37 25.04.2025 (የተሻሻለ: 12:54 25.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት በቀጣዩ የበጀት ዓመት ወደ 10 በመቶ ዝቅ እንደሚል የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ አስታወቀ
የባንኩ አስተዳዳሪ ማሞ ምሕረቱ ትናንት በዋሽንግተን በተካሄደው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትና ዓለም ባንክ ስብሰባ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የዋጋ ግሽበቱ በመጋቢት ወር 13 በመቶ መደረሱን ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ በእጥፍ ያድጋል ብለው እንደሚጠብቁ እና ከውጭ የሚላክ ገንዘብ በትንሹ በ25 በመቶ ሊጨምር እንደሚችልም ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከፍተኛ እድገት ማሳያቱን አስታውቀዋል፡፡
"ከማሻሻያው በኋላ የውጭ ምንዛሪ ክምችታችን በሦስት እጥፍ ጨምሯል። በባንክ ሥርዓቱ ያለው ክምችት በእጥፍ ጨምሯል፡፡ በኢኮኖሚው የካፒታል ፍሰት ላይ ግልፅ እድገት እና ጥንካሬ ይታያል" ብለዋል።