ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶቿን ለብሪክስ ሀገራት ማስተዋወቅ አለባት ሲሉ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ተናገሩ
11:47 25.04.2025 (የተሻሻለ: 12:04 25.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶቿን ለብሪክስ ሀገራት ማስተዋወቅ አለባት ሲሉ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ተናገሩ
ኖሴባ ናንሲ ሎሲ ይህን ያሉት የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን ከጎበኙ በኋላ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ነው፡፡
አምባሳደሯ የደቡብ አፍሪካ እና የኢትዮጵያ ጠንካራ የሁለትዮሽ ግኑኝነት በቱሪዝም ዘርፉም እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡
አክለውም "ሁለቱ ሀገራት የብሪክስ አባል እንደመሆናቸው፤ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቦታዎችን ለብሪክስ አባላትም ማስተዋወቃቸው ጠቃሚ ነው" ብለዋል፡፡
የቱሪዝም ሚንስቴር ከዩኔስኮ ጋር በመተባበር መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮች ባዘጋጀው የጉብኝት መርሃ ግብር ከ20 በላይ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል።
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በ2016 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በዓለም አቀፍ ቅርስነት መመዝገቡ የሚታወስ ነው፡፡