የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሪክስ ሀገራትን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እንደሚሠራ ገለፀ
21:09 24.04.2025 (የተሻሻለ: 21:24 24.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሪክስ ሀገራትን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እንደሚሠራ ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሪክስ ሀገራትን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እንደሚሠራ ገለፀ
ይህ የተገለፀው በዛሬው እለት በተከፈተው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ፎረም ላይ ነው።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ስብሰባ በዘርፉ በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ምክክር፣ የልምድ ልውውጥ እና ለጋራ ችግሮች የጋራ መፍትሄዎች እንደሚፈለጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው አየር መንገዱ የብሪክስ ሀገራትን የአየር ትራንስፖርት በማሳደግ ረገድ የበኩልን ሚና የሚጫወትበትን መንገድ እያጤነ እንደሆነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
"በብሪክስ ማሕበረሰብ ውስጥ ንግድ ለመጨመር እንቅስቃሴ አለ። በብሪክስ ህብረት ኩባንያዎች ሊተባበሩባቸው ከሚችሉባቸው መስኮች ውስጥ አንዱ የአየር ትራንስፖርት ኢንዱስትሪ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በብሪክስ ሀገራት መካከል የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን በማሳደግ ረገድ ሊጫወተው የሚችለውን ሚና በተመለከተ ጥናት እያካሄደ ነው። ይህንን ከሌሎች የብሪክስ አባላት ጋር በመሆን መዳሰሳችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
