ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቀረበ
17:29 24.04.2025 (የተሻሻለ: 17:44 24.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቀረበ
ፋብሪካው ምርቱን ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ እንዳቀረበ አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ ዓመት መጀመሪያ የመረቁት ይሄ ፋብሪካ ከ1 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
የፋብሪካው ምርት ገበያውን ከማረጋጋት ባሻገር በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ መነቃቃት ፈጥሯል ተብሏል።
በኢትዮጵያው ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግና በቻይናው ዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ በሽርክና የተገነባ ሲሆን በቀን አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ የማምረት አቅም አለው።